በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት

በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ሆኖ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-

  1. በሴቶች እና ህጻናት ላይ ጾታን ወይም እድሜን መሰረት አድርጎ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ምርመራ ይመራል፣ በምርመራ መዛግብት ላይ ህጋዊ ውሳኔ ይሰጣል፣ በፍርድ ቤቶች ክርክር ያደርጋል፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የወንጀሎቹ አያያዝ ዙሪያ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፣ 
  2. በፍትህ እና እንክብካቤ ማዕከላት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ይከታተላል፣ ዐቃቤ ህግ መመደቡን ይከታተላል፣ የማዕከላቱን የስራ ሪፖርት ለዘርፉ ኃላፊ እና ለሴቶች፣ ሕፃናት እና ባለ ብዙ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፤ 
  3. በሴቶችና ሕፃናት መብት ጉዳዮች የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በፍትህና እንክብካቤ ማእከላት ተግባራትን ያቀናጃል፣ ቋሚ የግንኙነት ስርዓት ይዘረጋል፣ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  4. ለሴቶችና ህጻናት ምርመራ ቡድኖችንና ስነልቦና ባለሞያዎች ድጋፍ ይሰጣል፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣
  5. በህፃናት ላይ የሚፈፀሙና ከሴቶች ጾታዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ወንጀሎች የመረጃ ስርዓት ያደራጃል፣ ለዕቅድ አፈፃፀምና ሪፖርት ግብአትነት ጥቅም ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣
  6. ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አስመልክቶ በቅንጅት ይሰራል
  7. በህፃናት ላይ የሚፈፀሙና ከሴቶች ጾታዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ወንጀሎች የመረጃ ስርዓት መሰረት መረጃ ይይዛል፣ ይተነትናል፣
  8. በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል የንቃተ ሕግ ስራ ከንቃተ ህግ ዳይሬክቶሬት እና ከሴቶች፣ ህጻናት እና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ይሰጣል፤
  9. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
  10. 10.ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  11. 11.ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  12. 12.የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
  13. 13.በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
  14. 14.ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  15. 15.ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
  16. 16.ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
  17. 17.የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
  18. 18.በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
  19. 19.የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤
  20. 20.በተጨማሪም ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል

በሴቶችእናህጻናትላይየሚፈጸሙወንጀሎችዝርዝር፡

በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ከላይ በተገለጸው አግባብ ጾታን ወይም እድሜን መሰረት ባደረገ ተጋላጭነት የሚፈጸሙ ከዚህ በታች የተመለከቱት የወንጀል አይነቶችን የሚመለከት ነው፡-

  1. በሰው ህይወት፣ አካልና ጤንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539-579)፤
  2. በሰው ነጻነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 580-606)፤
  3. በመልካም ፀባይ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620-661)፤
  4. በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀጽ 3፣ 4 እና 7 ላይ የተመለከቱ በሴቶች እና በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች

በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የስራ ክፍሎች ከሚታዩ ሌሎች የወንጀል ጉዳዮች ጋር የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች በተደራቢነት የሚገኝ በሚሆን ጊዜ ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትለው ጉዳይ በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ሆኖ ሲገኝ ክሱ በዚህ ዳይሬክቶሬት ተጠቃሎ ይታያል፡፡

የወንጀሎቹአይነትእናየሚታዩበትደረጃ፡

ከላይ ለማመላከት እንደተሚከረው በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በማዕከል እና በጽ/ቤቶች ደረጃ የሚታዪ ሲሆን በማዕከል የሚታዩት ጉዳዮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች የሚያሟሉ ሲሆኑ የተቀሩት ግን በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ደረጃ እየታዩ በዳይሬክቶሬቱ ክትትል እና ድጋፍ የሚሰረግባቸው ይሆናል፡-

  1. በህጻናት እና በሴቶች ላይ የተፈጸመው ወንጀል የተጎጂን ሕይወት ያሳጣ በሆነ ጊዜ ወይም፣
  2. በሁለት እና ከዚያ በላይ ክፍለ ከተማዎች ወይም ክልሎች ውስጥ የተፈጸመ ወይም ግንኙነት ያለው ጉዳይ ከሆነ ወይም፣
  3. በልዩ ሁኔታ የተፈጸመው ወንጀል የህዝብን ሞራል በከፍተኛ ሁኔታ የነካ እና ከፍተኛ የህዝብ ቁጣን ያስከተሉ ጉዳዮች ወይም፣
  4. በቅሬታ በማዕከል እንዲታዩ የታመነባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

Department Lead

ትእግሥት መሀቤ ሙሉአለም

ዳይሬክተር