የፍትህ ሚኒስቴር ያልተሰሙ የኋላ ታሪክ ክፍሎች 

1900
1900
የፍርድ ሚኒስቴር በ1900 ከተቋቋመ በኋላ በዳኝነት ሚኒስትር ደንብ መሰረት የዳኝነት ስራን እንሰዲራ ተደረገ፡፡ የሚኒስትሩ የይግባኝ ሰሚነት በወንጀል እና በፍትሐ ብሔር ጉዳይ የፍትሐ ነገስትን መሰረት በማድረግ ነበር የሚካሄደው
1900
1900
1900
ጥቅምት 15/1900 ዓ.ም ከተሾሙ 10 የመጀመሪያ ሚኒስትሮች መካከል የፍርድ ሚኒስትር አንዱ ነበር። አስቀድሞ በአገሪቱ አራት ዋና ዋና የስራ መሪዎች በነበሩ ጊዜ የዳኝነት ጉዳይ የሚመለከታቸው አፈ-ንጉሱን ነበር፡፡ የፍትሕ ሚኒስትሩ ሲሾሙ የሚኒቴር መስርያ ቤት አልነበረም፤ይልቁንም ሚኒስትሮቹ ተቋሙን እንዲያቋቋሙ ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡
1900
1900
1900
ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም የፍርድ ሚኒስትሩ ከተሾሙ በኋላ ለአንድ ሚኒስትር ስራው ስለሚበዛ በሚል አጋዥ 12 ወንበሮች እና 6 ችሎቶች ተጨምረው ነበር፤
1900
1910
1910
በ1910 ዓ.ም ህዝቡ ቅሬታ በማቅረቡ ምክንያት በጃን ሜዳ በተካሄደ ጉባኤ ሚኒስተሮቹ እንዲሻሩ ሲደረግ ከተሻሩት መካከል የፍርድ ሚኒስትር አንዱ ነበር።
1910
1922
1922  ዓ/ም ሚኒስተሮች መስርያ ቤት እንደገና እንዲቋቋም ተደረገ
የግድያ ወንጀል በሚመለከት ጉዳዩ በአውራጃ ዳኞች ተጣርቶ ለወንጀል ቅጣት ፍርድ ቤት እንዲተላለፍና የወንጀል ቅጣት ፍርድ ቤትም ምርመራውን አሟልቶ አጠናክሮ ለዋናው ችሎት /ንጉሡ ወይም አልጋ ወራሹ ለሚያስችሉበት/ ይቀርብ ነበር፤ ይህም በደንብ የጸደቀ ነበር፡፡ በወቅቱ ፍትህ ሚኒስተር የወንጀል ምርመራን ደርቦ ይሰራ ነበር፤ ቀደም ብሎ ወንጀል ተለይቶ ለመንግስት ተሰጥቶ ስላልነበር ምርመራም ሆነ ሙግት በተፋላሚዎች ወይም በዘመዶቻቸው ነበር ይደረግ የነበረው ሟች ዘመድ ያልነበረው እንደሆነ የወህኒ ቤት ዘበኞች ሹም ስለ ሟች እንዲሞግት ደይረግ ነበር። በኢትዮጵያዊ እና በውጭ አገር ዜጎች መካከል የሚነሳን ክርክር በሚመለከት ይግባኝ ሰሚው ንጉሱ በሚሰየሙበት ይሰየም ነበር፡፡
1922
1923
1923
ታህሳስ 2/1923 የምህረት አዋጁን የማስፈጸም ተግባር ለፍርድ ሚኒስትር ተሰጠ።
1923
1923-1933
1923-1933
ንጉሱ ወደ ውጭ ሀገር ከሄዱበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1933 የውጭ ወረራ ስለነበር ሀገሪቱ መንግስትም፤ ሚኒስትርም አልነበራትም
1923-1933
1923-1933
1934
የንጉሱን መመለስ ተከትሎ በ1934 ዓ.ም ነጋሪት ጋዜጣ ተቋቋመ፡፡ በዚህም መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ የዳኝነት ስራ በአዋጅ ቁጥር 2/1934 ታወጀ፡፡ አዋጅ ቁጥር 1/1934 ነጋሪት ጋዜጣው የተቋቋመት አዋጅ ነበር፡፡
1923-1933
1935
1935
የዐቃብያነ ህግ አዋጅ ወጣ፤ ዐቃቤ ህግን በበላይነት የሚመራው የፍርድ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ሲሆን በወንጀል ጉዳይ መንግስትን ወክሎ መከራከር የሚያስችል ስልጣን ተሰጠው፡፡ ዐቃቤ ሕጎች በዋና ዐቃቤ ህግ እና በምክትል ዋና ዐቃቤ ህጎች ይመሩ ነበር፡፡ የዋና ዐቃቤ ህጉ ስራ ዐቃቤ ህግን በማሰማራትና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በመንግስት ስም ጠበቃ በማቆም  በማናቸውም የወንጀል ጉዳይ የመከራከር ስልጣን ተሰጥቶት ነበር፡፡

የፍርድ ሚኒስቴር በተቋምነት በህግ ይፋ የሆነው በትዕዛዝ ቁጥር 1/1935 አንቀጽ 22 መሰረት ነው። ስልጣንና ተግባሩ በአንቀጽ 59 እስከ 61 ተዘርዝሯል፡፡ 
1935
1938
1938
ሁለት የውጭ ሀገር ተወላጆች በጠቅላይ ዐቃቤ ህግነት ተሹመው ሰርተዋል፡፡
1938
1943
1943
የዐቃቤ ህጉን ክፍል የሚመራው ባለስልጣን ዐቃቤ ህግ ተብሎ እንዲሰየም ተወሰነ
1943
1945
1945
የፍርድ ሚኒስተሩ የፌዴራሉን መንግስት የፍትህ አስተዳደር የመቆጣጠር ስልጣን ተሰጥቶታል 
1945
1948
1948
ሚኒስትሩን ከማማከር ስራው በተጨማሪ በፓርላማው ጥሪ ሲደረግለት ቀርቦ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ያቀርብ ነበር፡፡ 
1948
1949
1949
የወንጀል ህግ የወጣ ሲሆን  ማንኛውም የወንጀል ክስ ለዐቃቤ ህግ መቅረብ እንዳለበት በእርቅ ቢያልቅ እንኳ ዐቃቤ ህግ ተከታተሎ የማስወሰን ግዴታን ጥሎበታል
1949
1954
1954
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት የወንጀል ህግ በትዕዛዝ እንዲነሳ የማድረግ ስልጣንን ይዞ መጣ፡፡ 
1954
1958
1958
ከፍትሀ ብሄር ረገድ ደንብ ለማውጣት የሚያስችል ሥልጣን እውን ሆነ፡፡ 
1958
1965
1965
የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የተቋቋመ ሲሆን የጉባኤው ሰብሳቢ የፍትህ ሚኒስትር ነበር፡፡ 

ለክልል ግዛት ገዢዎች የዳኝነት ስልጣን የሰጠው ህግ የተሻረው በ1965 ዓ.ም ነው።
1965
1967
1967
ልዩ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ወጥቶ በልዩ ፍርድ ቤት እና ዐቃቤ ህግ ይታይ ጀመረ፡፡
1967
1969
1969
ደርግ የ 1935ቱን የሚኒስተሮች ሥልጣንና ተግባር መሰረት የፍትህ አስተዳደርን በሀላፊነት የሚመራው አካል  “የፍርድ ሚኒስቴር” መባሉ ቀርቶ “የህግና ፍትህ ሚኒስቴር” ተባለ
1969
1985-1986
1985-1986
የሽግግር መንግስቱ የ1985 በወጣው አዋጅ መሰረት ሲሰራ ቆይቶ በ1986 ዓ.ም የአዋጅ ቁጥር 73/86 የማዕከላዊ ዐቃቤ ህግ መስርያ ቤት ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር የተዋሀደ ሲሆን የመንግስት የህግ አማካሪነት፣ የብሄር ብሄረበቦችንና ህዝቦችን መብት ማስጠበቅ፣ የወንጀልንና የፍታብሄር ህጎችና ማስጠበቅ፣ የህግ ረቂቅ ማሰባሰብና ማጠቃለል እንዲሁም የማከማቸትና የትርጉም ስራዎችን መስራት በተጨማሪነት የተሰጡ ተግባራት ነበሩ
1985-1986
2008
2008
2008 ዓ.ም ላይ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት በገቢዎች እና ጉምሩክ፣ በጸረ ሙስና ኮሚሽን እና ሸማቾች ዐቃቤያነ ህግ ሲመሩ የነበሩ የዐቃቤ ህግነት ስራዎችን በመጠቅለል መጠሪያው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሆኖ በአዲስ መልክ ተቋቋመ
2008
2014
2014
በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረትም ስያሜው ወደ ቀድሞ ስያሜው ፍትሕ ሚኒስቴር እንዲመለስ ተደረገ፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረትም የሸማቾች እና የምርት ገበያ አስተዳደራዊ ችሎቶችም ፍትህ ሚኒስቴር ስር እንዲወድቁ ተደረገ
2014
የዳኝነት ስራ በመደበኝነት በፍርድ ቤት መሰራት ከመጀመሩ በፊት የግዛት ክልሉ ገዢ በፍርድ ቤት ሰብሳቢነት የዳኝነት ስራን ያከናውን ነበር፤
የመጀመሪያው  የፍርድ ሚኒስተር አፈ ንጉሥ ነሲቡ መስቀሉ ነበሩ
ፍትህ ሚኒስቴር ስያሜውን በሚመለከት፤ ፍርድ ሚኒስተር፣ የዳኝነት፣  ህግና ፍትህ ሚኒስቴር፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሚሉ ስያሜዎች ይጠራ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ፍትሕ ሚኒስቴር ተብሎ ይጠራል፡፡