የወንጀል ስነ ስርአት እና ማስረጃ ሕግ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት

የወንጀል ስነ ስርአት እና ማስረጃ ሕግ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ ለረጅም አመታት ስራ ላይ የቆየው የወንጀል ስነ ስርአት ሕግ በአዲስና ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ በመሰረቱ በመከለሱ በሕጉ መሰረት መውጣት ያለባቸውን ተጨማሪ ሕችን፣ደንቦች መመሪያዎችና አሰራሮች ለማዘጋጀት፣መቋቋም ያለባቸው ተቋማት ለማቋቋም፣ሕጉን ለማስረፅ፣የሕጉን ፈፃሚ አካላት ለማስተባበር ካለው የስራ ስፋት አንፃር እራሱን ችሎ ሲደራጅ በስሩም የሕጎች ዝግጅትና ስርፀት ቡድን እና የፈጻሚና ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ቡድን የያዘ ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

  1. የወንጀል ስነስርዓትና ማስረጃ ሕግ ለማስተግበር ፕሮጀክት ይቀርፃል፣ሲፀቅድቅ አፈፃጸሙን ይከታተላል፣ 
  2. የወንጀል ስነስርዓትና ማስረጃ ሕግን ለማስተግበር የሚረዱ ሕጎች፣ አሰራሮችና ፕሮግራሞች ይቀርፃል፣ በሚመለከታቸው አካላት ሲፀድቁ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ 
  3. የወንጀል ስነስርዓትና ማስረጃ ሕግ ለማስተግበር መቋቋም ያለባቸው ተቋማት ይለያል፣የማቋቋምያ ጥናት ያካሂዳል፣ተቋማቱ መቋቋማቸው ይከታተላል፣ 
  4. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የወንጀል ስነስርዓትና ማስረጃ ሕግ ዙሪያ ለሁሉም መርማሪዎችና ዐቃቤያነሕግ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የስራ ላይ ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፣ 
  5. የወንጀል ስነስርዓትና ማስረጃ ሕግ ትግበራ ቅንጅትን ለማጠናከር የሕጉን ፈፃሚ አካላት ያስተባብራል፣
  6. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  7. ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  8. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  9. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  10. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት አንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  11. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  12. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  13. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  14. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  15. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  16. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

ትእግሥት መሀቤ ሙሉአለም

ዳይሬክተር