ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት

ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ በተሻሻለው አዋጅ መሰረት መጠነኛ መጠሪያ ለውጥ በማድረግና በተልእኮ ግልፀኝት የቡድን ክፍፍል በመፍጠር በስሩ ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ሴክሬተሪያት እና የሕግና እና ፖሊሲ ማስተግበሪያ ክትትል ቡድን በመያዝ የተደራጀ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡- 

  1. በሰው የመነገድ፣ ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር እና በሕገ ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ለመከላከል የተቋቋመ የብሔራዊ የትብብር ጥምረት ተግባርና ኃላፊነቱን እንዲወጣ ይደግፋል፣ የሴክሬቴሪያት አገልግሎት ይሰጣል፣ 
  2. ሀገራዊ የፍልሰት ፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  3. የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የተጋላጭነት ሁኔታ ከቦታ፣ከተጎጂዎችና ከአዘዋዋሪዎች አንጻር ጥናት ያካሄዳል፣ የተጋላጭነት ካርታ ያዘጋጃል፣ ለተጠቃሚዎች ያደርሳል፣ 
  4. አዋጁን ለማስፈፀ፣ የሚያስፈልጉ ደንቦችና መመሪያዎች መውጣታቸውን ያረጋግጣል፣ 
  5. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የአዋጁ ሃገራዊ ተፈፀሚነት በአዋጁና አፈፃፀሙ ዙሪያ ሃገራዊ ንቅናቄና ግንዛቤ ይፈጥራል፣ 
  6. የህገወጥ የሰዎች ዝውውር የወንጀል ፈፃሚዎችን ተጠያቂነት ሁኔታ መረጃ ማዕከል ያቋቁማል፣ መረጃ ያደራጃል፣ይተነትናል፣ ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል፣ 
  7. ሀገራዊውን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመከላከል ከክልል አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት ይሰራል፣ 
  8. የጥምረቱንና የሥራ ቡድኖች እቅዶችና ስራዎች ከሀገራዊ አጠቃላይ ስትራቴጅዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ከህጎችና አለማቀፍ ሰነዶች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ይከታተላል እንዲሁም ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ 
  9. ጥምረቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብበር የሚሰራበትን ሁኔታ ያስተባበርል፣ 
  10. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  11. ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  12. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  13. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  14. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
  15. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  16. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  17. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  18. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  19. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  20. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

አብርሀም አያሌው ይመር

ዳይሬክተር