የጥብቅና ፍቃድ አስተዳደር እና ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

የጥብቅና ፍቃድ አስተዳደር እና ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ ትኩረት በሚፈልገው የጠበቆች አገልግሎትና ስነምግባር ክትትልን ልዩ ትኩረት በመስጠት የቡዱን አደረጃጀቱ የተሻሻለ ሲሆን በድሬዳዋ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የጠበቆች ፍቃድ እድሳትና የክትትል ተግባር እና አደረጃጀት በቡድን ደረጃ እንደሚኖር ታሳቢ በማድረግ ሲደራጅ በስሩም የጥብቅና ፍቃድ እና እድሳት ቡድን፣የጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ እና ሙያ ስነ-ምግባር ክትትል ቡድን እና የነጻ የሕግ ድጋፍ አግልግሎት ቡድን በመያዝ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  1. የጥብቅ ፈቃድ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፍ ማስፈፀምያ መመርያና አሰራር ያዘጋጃል፣ሲፀድቅ ያስፈጽማል፣ 
  2. የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ የስነምግባር ቅድመ ማጣሪያ ስርዐት ይዘርጋል፣ ይተገብራል፣
  3. በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ደረጃ የጥብቅና አገልግሎት ለሚሰጡ ጠበቆች በሕግ መሠረት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ጠበቆችንና የጥብቅና አገልግሎትን ያስተዳድራል፣ይቆጣጠራል፤ 
  4. የጠበቃ ረዳትና የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ ይመዘግባል፣ ለሚመለከተው ያሳውቃል፣ 
  5. በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ደረጃ የጥብቅና አገልግሎት ለሚሰጡ ጠበቆች በሕግ መሠረት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ጠበቆችንና የጥብቅና አገልግሎትን ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፤ 
  6. ጠበቆች ስነ-ምግባር ዲሲፒሊን ዉሳኔ አሰጣጥ ቅልጥፍና ጥራት ማረጋገጥ የሚያስችል አሰራር ቀርፃል፣ ይተገብራል 
  7. በጠበቆች ላይ የዲስኘሊን ክስ ያቀርባል፣ከተገልጋዮች የክስ አቤቱታ ይቀበላል፣ወክሎ ክስ ለጉባኤ ያቀርባል፣እስከ ሰበር ይከራከራል፣ውሳኔዎች ያስፈፅማል፣ 
  8. የጠበቆች የአገልግሎት አሰጣጥ፣የሙያና የስነምግባር ብቃት ለማሳደግ፣ከሚመለከታቸው ጋር ይሰራል፣ 
  9. የጥብቅናው ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥና የስነምግባር ሁኔታ የተገልጋዮች/ደንበኞች አመኔታ እያረጋገጠ ስለመሆኑ ይከታተላል፣ 
  10. የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ አፈፃፀም በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን ያስተባብራል፣አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  11. የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስርዓት ይዘረጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  12. የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ተገልጋዮች እርካታ ደረጃ መለኪያና አሰራር ይቀርፃል፣በየወቅቱ ይለካል፣ 
  13. የገንዘብ አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የሕግ ምክርና የጥብቅና አገልግሎት እንዲያገኙ ለጠበቆች ይመራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  14. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  15. ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  16. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  17. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  18. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  19. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  20. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  21. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  22. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡድኖች ሪፖርት ይቀበላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  23. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  24. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

ፍቃዱ ደምሤ አለሙ

ዳይሬክተር