ሚኒስትር ጽ/ቤት

የሚኒስትር ጽ/ቤት ቀደም ሲል የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በሚል የተደራጀ ሲሆን በስሩ የህግ አማካሪዎች እና የቅሬታ አጣሪ ቡድን፣ የተጠሪ የስራ ክፍሎች እና ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ቡድን እንዲሁም የሥነ ምግባር ክትትል ቡድንን በስሩ ይዞ የሚከተሉት ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡

  1. ፍትህ ሚኒስትሩን ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ያማክራል፤ አማካሪዎችንና የአስተዳደር ሰራተኞችን ያስተባብራል፣ ያሰማራል፣ የስራ አፈፃፀማቸውን ይገመግማል፣ ይመዝናል፤ 
  2. ፍትህ ሚኒስትሩ በመደበኛ ስብሰባና ከመ/ቤቱ ውጭ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በማይገኝበት ጊዜ ወክሎ ይሳተፋል፣ ለተለያዩ ስብሰባዎች እና ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ንግግሮችን ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ 
  3. የበላይ አመራሩ ለሚሳተፉባቸው ብሔራዊና አለም አቀፍ ስብሰባዎች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እና መግለጫዎች ተሟልተው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤ 
  4. ለፍትህ ሚኒስትሩ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ ይሰጣል ፣ በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች የውሳኔ ሓሳብ ያቀርባል፣ 
  5. የማኔጅመንት ስብሰባዎችን ያቀናጃል፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመመካካር አጀንዳ ይቀርፃል፣ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ በአግባቡ መያዙን ያረጋግጣል፣ የተሰጡ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎችን ተፈጻሚነት ይከታተላል፤ 
  6. የፍትህ ሚኒሰቴር እና የክልል ፍትህ ቢሮ የጋራ መድረክ ፀሐፊ ሆኖ ያገለግላል፣ ያስተባብራል፣ ከፍትህ ሚኒስትሩ በሚሰጠው አቅጣጫ አጀንዳ ይቀርፃል፣ 
  7. ከሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን በመቀበል እንዲጣራ ለሚመለከተው አካል ይመራል፣ ተጣርቶ ሲቀርብም መርምሮ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ውሳኔ ያቀርባል፣ 
  8. ለበላይ አካላትና ለተለያዩ መ/ቤቶች የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ይከታተላል፣ ግብረመልስ ይሰጣል፣ 
  9. ለተቋሙ ተልዕኮ ማሳካት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፤ 
  10. በመ/ቤቱና በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚደረጉ የቅንጅት ስራዎች ያስተባብራል ፣የመግባቢያና የፕሮቶኮል ስምምነት ሰነዶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ያስፈጽማል፣ 
  11. በፍትህ ሚኒስትሩ ሰብሳቢነት የሚመሩ ቦርዶችን፣ ግብረኃይሎችን እና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ይከታተላል፤ ይደግፋል፣ 
  12. ከተለያየ አካላት የሚቀርቡ አስተያየቶችን ምርምሮ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተጠቃለለ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል ፣ የተሰጡ ውሳኔዎች አፈፃፀም ይከታተላል፣ 
  13. የተጠሪ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርና ቋሚ የክትትልና ድጋፍ ስርአት ይዘረጋል፣ 
  14. በተጠሪ ተቋማት የሚወጡ ህጎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ፕሮግራሞችንና ዕቅዶችን ይከታተላል፣ 
  15. ለፍትህ ሚኒስትር ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎችን ያቀናጃል፣ ያስተባብራል፣ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ላይ ግብረ መልስ ይሰጣል፤ 
  16. ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ተልዕኳቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ይከታተላል፣ ለሚያቀርቡት ጥያቄ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጣቸው ያደርጋል፣ 
  17. ከስራ ዘርፎች፣ ከተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ከተለያዩ አካላት ለበላይ አመራሩ የሚላኩ ጉዳዮችን ምላሸ ይሰጣል፤ ውሳኔ የሚሹትን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀርባል፤ 
  18. በፍትህ ሚኒስትር ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ከሕግና መ/ቤቱ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አንፃር በመለየት በማስረጃ ተደግፈው እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ ውሳኔ ሲያገኙ ተፈጻሚነታቸውም ክትትል ያደርጋል፣ 
  19. ለፍትህ ሚኒስትር መቅረብ ያለባቸው ጉዳዮች ቀጠሮ እንዲያዝላቸው ያደርጋል፣ጉዳዮችን በመለየት የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል ሲወሰንም ተፈጻሚነታቸውም ይከታተላል፣ 
  20. ለፍትህ ሚኒስትር እና ለጽ/ቤቱ የተመደበን በጀት ያስተዳድራል፣ ተለይቶ በሚሰጠው ዉክልና፣ ግዢ ወይም ክፍያ እንዲፈጸም ለሚመለከተው ጥያቄ ያቀርባል፣ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚያስፈልግ ግብአት መሟላቱን ያረጋግጣል፣ 
  21. በፍትህ ሚኒስትር የሚከናወኑ የጽሑፍ ግንኙነት፣ የስብሰባና የጉዞ ፕሮግራሞችን ይመራል፣ 
  22. የፍትህ ሚኒስትር የስብሰባ መርሃ ግብር እና ግዜ ሰሌዳዎች ያቀናጃል፣ 
  23. የፕሮቶኮል ሽፋን መሰጠት ለሚያስፈልጋቸው የበላይ አመራሮችና የውጭ እንግዶች መሰጠቱን ያረጋግጣል፣ 
  24. የበላይ አመራሩ የእንግዳ መስተንግዶ እና የሀገር ውስጥና የውጭ አገራት ጉዞ ዝግጅቶች አፈፃፀም ያመቻቻል፣ ይከታተላል፣ 
  25. ከዚህ በፊት የሕግ ኦዲት ቅሬታና ስነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት በደንብ ቁጥር 443/2011 አንቀጽ 91/2 ተሰጥቶ የነበረዉን የዲስፕሊን ጥፋት ሲፈፀም ለዋና ጉባኤ ወይም ለንኡስ ጉባኤዉ ክስ እንዲቀርብ ያደርጋል፣ 
  26. የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ የሚገባቸዉን አመራሮችና ሰራተኞች ሃብታቸዉን ይመዘግባል፣ የምዝገባ ሰነዱን ለሚመለከተዉ መ/ቤት በወቅቱ መላኩን ይከታተላል፣ 
  27. ሀብታቸዉን ያስመዘገቡ አመራሮችና ሠራተኞች ወቅቱን ጠብቆ እድሳት እንዲያደርጉ ይከታተላል፣ ሲለቁ ክሊራንስ ከማግኘታቸዉ በፊት ዳግም ምዝገባ እንዲያካሂዱ ያከታተላል ፣ እሴቶችና የስነምግባር ደንቦች ማስረጽና ማስፈጸም የሚያስችሉ ስልቶች ይቀርፃል፣ መተግበሩን ይከታተላል፣ 
  28. ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጡ የስራ ክፍሎችንና ክፍተቶችን በጥናት በመለየት የመከላከያ ስትራቴጂ እንዲቀረፅ ያስተገብራል፣ ይታተላል፣ 
  29. ተቋማዊና የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ እንዲቀረፅ ያደርጋል፣ 
  30. ለተቋሙ ሰራተኞች የስነ-ምግባር ስልጠና እንዲሰጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፣ 

Department Lead

ምስክር ታሪኩ ይረፉ

የጽ/ቤት ሃላፊ