የብሄራዊ ሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀ-ግበር ፅ/ቤት

የብሄራዊ ሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀ-ግበር ፅ/ቤት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ ከዚህ ቀደም ከነበረው የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀ-ግብር አፈፃፀም ክትትል ተግባርና ኃላፊነት በተጨማሪ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደሩ ያለውን የተያዙና በሕግ ቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች ሰብአዊ መብት አያያዝና አጠባበቅ ክትትል የማድረግ ሆኖ በስሩም የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀ-ግብር አፈፃፀም ክትትል ሴክሬተሪያት እና በወንጀል ፍትህ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ እና አጠባበቅ ክትትል ቡድን ይዞ ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡ 

  1. ብሔራዊ የሰብአዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብርን ከሚመለከታው አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም አፈፃፀሙን ይከታተላል፤የሚመለከታቸውን አካላት ያስተባብራል፣ሪፖርት ያቀርባል፤ 
  2. በድርጊት መርሃ ግብሩ ይዘትና አፈፃጸም ሃገራዊ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያደርጋል፣ 
  3. በጽ/ቤቱ፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በወንጀል ገዳዮች የዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬቶች የሰብዓዊ መብት ጥበቃ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ ስርአት ይዘረጋል፣ክትትል ያደርጋል፣ በየወቅቱ ሪፖርት እንዲቀርብለት ያደርጋል፣ 
  4. የተያዙ፣ የተከሰሱ፣ በሕግ ቁጥጥር ስር የሚገኙና የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አከባበርና በሕግ መሰረት መሆኑን ያረጋግጣል፣ 
  5. በፖሊስ ጣቢያና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎችን በመደበኛት ወይም በድንገት ይጎበኛል፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፣ ሕገ ወጥ ተግባር እንዲታረም እንዲሁም ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤ 
  6. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  7. ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  8. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  9. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  10. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤ የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  11. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  12. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  13. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  14. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  15. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  16. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

አወል ሱልጣን መሀመድ

ዳይሬክተር