የይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት ተግባር እና ኃላፊነት

የይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ጽ/ቤት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የተደራጅ የስራ ክፍል ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ሃለፊነት ይኖሩታል፡- 

  1. ከሕግ ታራሚዎች እና ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሚቀርቡ የይቅርታ ጥያቄን በመመርመር ለይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ያቀርባል፣ 
  2. የቦርድ ውሣኔ ሃሣብና ይቅርታ የሚገባቸዉን ታራሚዎችን ዝርዝር መግለጫ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀርባል፣ 
  3. የይቅርታ ዉሳኔዎችን ለታራሚዎች እና ለማረሚያ ቤት ያሳውቃል፣ በውሳኔ መሰረት መፈፀሙን ይከታተላል፣ 
  4. ከክልሎች የቀረቡ ፌዴራል ጉዳይ ታራሚዎች የክልል የቦርድ የዉሳኔ ሀሳብ ለፌደራል ይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ያቀርባል፣ በውክልና በተሰጡ ጉዳዮች ይቅርታ አሰጣጥ ክትትል ያደርጋል፣ 
  5. በተጭበረበረ ማስረጃዎች በይቅርታ የወጡ ታራሚዎች ጉዳይ መርምሮ ለቦርድ የውሣኔ ሐሳብ ያቀርባል፣ 
  6. የፌዴራልና የክሎች የይቅርታ አሰጣጥ ተቀራራቢ እና ተናባቢ እንዲሆን ለክልሎች የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጋራ መድረክ ያቀርባል ፣ 
  7. በይቅርታ አሠጣጥ ዙሪያ የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎች ያጣራል፣ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጣቸው የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፣ 
  8. ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመመካከር የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  9. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  10. ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  11. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  12. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  13. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  14. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  15. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  16. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  17. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  18. በስራ ክፍሉ ተልእኮ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  19. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

ሠናይት እንየው ቦጋለ

ዳይሬክተር