የፍትህ ስርአት ማሻሻያና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት

የፍትህ ስርአት ማሻሻያ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሚኒስትር ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  1. የተቋሙን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
  2. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  3. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
  4. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
  5. ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፅ/ቤት ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  6. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
  7. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
  8. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
  9. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
  10. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤
  11. በፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም በተቋሙ እንዲተገበር ያስተባብራል፣
  12. የተቋሙ አገልግሎት በቴክኖሎጂ ታገዞ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፣ 
  13. የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የቅሬታና አስተያየት አቀራረብ ሥርዓት ቀርጾ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ የተገልጋዩን እርካታ ደረጃ መለኪያ ይቀርፃል፣ ይለካል፣
  14. የተተኪ አመራር መመልመያ ስርዓት ይዘረጋል፣ የመረጃ ቋትም ያደራጃል፣
  15. የመልካም ተቋማዊ ባህል ግንባታ ማዕቀፍ ይቀርፃል፣ እንዲተገበር ያስተባብራል፣
  16. ተቋማዊ አደረጃጀት ማሻሻያ ጥናት ያካሂዳል የማሻሻያ ሐሳብም ያቀርባል፣
  17. ከተቋሙ ተልእኮ አንፃር የለውጥ መሳሪያዎች ይለያል ፣ይቀርፃል ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፣ በአተገባበሩ ላይ ቴክኒካዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
  18. ምርጥ ተሞክሮ መቀመሪያ ስርዓት ይቀርፃል፣ተሞክሮ ይለያል፣ምርጥ ተሞከሮ ይቀምራል፣ ያስፋፋል፣
  19. የተቋም፣ የቡድንና የሰራተኞች የስራ አፈጻጸም መመዘኛ ይቀርፃል፣ መተግበሩን ይከታተላል፣ የተሻለ አፈፃጸም ላስመዘገቡ አካላት እዉቅናና ሽልማት እንዲያገኙ ያደርጋል፣
  20. ተቋማዊ የለዉጥ የተግባቦት ስርዓትን ይቀርፃል እንዲተገበር ያርደርጋል፣ 
  21. ከሌሎች የስራ ክፍሎች የሚቀርቡ የፕሮጀክት መነሻ ኃሳቦችን ይቀበላል፣ የሃብት ማፈላለጊያ ፕሮጀክቶችን መነሻ ሃሳብ ያዘጋጃል ወይም ለሚያዘጋጁ አካላት ድጋፍ ይሰጣል፣ 
  22. ከተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት በመነሳት አጋርና ለጋሽ ድርጅቶች መለያ መስፈርቶችና የትብብር መስኮች ማዕቀፍ ያዘጋጃል አተገባበሩን ይከታተላል፣
  23. ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጅዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  24. ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ቴክኒካዊ እና የገንዘብ ድጋፍ እድሎችን ያፈላልጋል፣ ይለያል፣ የድጋፍ ጥያቄ ያቀርባል፣
  25. የፍትህ ስርዓቱን የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች አተገባበር ዙሪያ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል፣
  26. የፕሮጀክቶችን አጠቃላይ ዕቅድና ትግበራ ያስተባብራል በተለይም በስትራቴጅክ ዕቅድ የተለዩ ፕሮጀክቶች ቀረፃና ሃብት ማሰባሰብ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ክትትል እና ድጋፍ ያዳርጋል
  27. የፕሮጀክቶች አፈፃፀም መለኪያ ውጤታማነት ክትትልና የግምገማ ስርዓቶችን ይቀርፃል ይተገብራል፣ለፕሮጄክቶች ስኬታማነት የተጽዕኖ ግምገማ ያዘጋጃል ይተገብራል፣
  28. የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
  29. በተጨማሪም ከሚኒስትር የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል፤

Department Lead

በረከት ማሞ ኤልታሞ

የጽ/ቤት ሃላፊ